ሥራ ፈጣሪ ትውልድ ለመገንባት የሁሉንም አካላት ትብብር ይጠይቃል።

2
ባሕር ዳር: ኅዳር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሥራ እና ክህሎት ቢሮ “በጋራ እንገነባለን” በሚል መሪ መልዕክት ዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ንቅናቄ ሳምንት የውይይት መድረክ ከአጋር አካላት ጋር እያካሄደ ነው።
የአማራ ክልል የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኀላፊ አማረ ዓለሙ ኢትዮጵያ በላቀ ፍጥነት እየተጓዘች ነው ብለዋል። የአማራ ክልል ሥራ እና ክህሎት ቢሮ በዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ንቅናቄ ሳምንት ለ87 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየሠራ ነው ብለዋል።
የዚህ ዓመት ዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ነው ያሉት።
የአስተሳሰብ እና የክህሎት ግንባታ ማስደግ፣ መደበኛ ኢንተርፕራይዞችን ማፍራት፣ ከፋይናስ ጋር ጠንካራ ድልድይ መፍጠር እና በውይይት ጠንካራ ሥነ ምህዳር መገንባት የዚህ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው ብለዋል።
ዕቅድ ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ወረቀት ላይ ያለ የተቀረጸ ሃሳብ ብቻ ነው ያሉት ምክትል ኀላፊው ሁሉም የየራሱን ተግባር እና ኀላፊነት በአግባቡ እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል።
የአማራ ክልል የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኀላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ.ር) ዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሳምንትን ስናከብር ያለንን ሃብት መነሻ አድርገን ሥራ ፈጣሪ ትውልድ መገንባት አለብን ብለዋል። ሥራ ፈጣሪ ትውልድ ለመገንባት የሁሉንም አካላት ትብብር ይጠይቃል ነው ያሉት።
ዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሳምንት ንቅናቄ ዓላማ ሥራ ፈላጊ ሳይኾን ሥራ ፈጣሪ ትውልድ ለመገንባት ነው ብለዋል።ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳየቷንም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ ሰመሀል ፍስሀ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleዘር አምራች አርሶ አደሮችን በማኅበር ለማደራጀት እየሠራ መኾኑን የወልድያ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
Next articleየአፈር ለምነትን እና ምርታማነትን ለማሻሻል ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው።