የአማራ ክልል ባለፈው በጀት ዓመት 120 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርቧል።

3
አዲስ አበባ: ኅዳር 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፈው በጀት ዓመት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 120 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረቡን የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
ሲሚንቶ፣ ከሰል እና ብረትን ጨምሮ ከ40 በላይ ማዕድናትን በክልሉ የማልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን ቢሮው ገልጿል።
የአማራ ክልል የማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ታምራት ደምሴ የአማራ ክልል ቀደም ባሉት ዓመታት የማዕድን ሃብቱ የኢኮኖሚ ፋይዳ ዝቅተኛ ነበር ብለዋል። የሀገሪቱን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ ዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል። ማዕድናቱንም ለኢንቨስትመንት ዝግጁ የማድረግ ሥራዎች ተከናውነዋል ነው ያሉት።
በክልሉ የሲሚንቶ፣ የድንጋይ ከሰል እና ሌሎች ማዕድናትን በስፋት የማልመት ሥራ እየተከናዎነ መኾኑንም ተናግረዋል።
ክልሉ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2017 በጀት ዓመት 120 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረቡን ገልጸዋል።
በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ ማዕድን አልሚዎች ክልሉ የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ እና የተመቸ መሠረተ ልማት ማዘጋጀቱንም አንስተዋል።
ዘጋቢ:- ኢብራሒም ሙሐመድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleወሳኞቹ የእርግዝና ወራት የትኞቹ ናቸው?
Next articleለመማር የሚታትሩ ተማሪዎች እና ለማስተማር የሚተጉ መምህራን ትምህርትን በውጤት ያጅባሉ።