
አዲስ አበባ: ኅዳር 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰመራ ሎጊያ ከተማ የሚካሄደው የከተሞች ፎረም ሁለተኛ ቀኑን ይዟል። በፎረሙ የተለያዩ ሁነቶች በመሥተናገድ ላይ ናቸው።
በፎረሙ ዙሪያ አስተያየት የሰጡት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በ10ኛው የከተሞች ፎረም ከ143 በላይ ከተሞች በመሳተፍ ላይ ናቸው ብለዋል።
ከ7 ሺህ በላይ የፎረሙ ተሳታፊዎች በሰመራ ሎጊያ ከተማ ተገኝተዋል ያሉት ሚኒስትሯ ከተሞችን ዋና ሀብት አመንጭ በማድረግ የእድገት እና የብልጽግና ማዕከል ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን አስታውቀዋል።
የከተሞችን ፕላን በአግባቡ በመተግበር እያንዳንዱ የመኖሪያ ቤት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲኖረው ለፕላን አተገባበር የተለየ ትኩረት መሰጠቱም ገልጸዋል።
በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች የፖናል ውይይቶች በመካሄድ ላይ ናቸው። የተለያዩ ከተሞችም ያሏቸውን ተሞክሮዎች ይዘው ቀርበዋል። የፈጠራ ሥራዎች፣ የኮሪደር ልማት አፈፃፀማቸው ያለበትን ደረጃ ከተሞች በኤግዚቢሽኑ በማስቃኘት ላይ ናቸው።
ዘጋቢ:- ተመስገን ዳረጎት
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
