በኢትዮጵያ ተጨማሪ 109 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የአንድ ሰው ሕይወትም አልፏል፡፡

233

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 09/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 102 ሰዎች በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ በ109 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በሀገሪቱ እስከ ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችም 3 ሺህ 630 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ከ1 እስከ 78 ዓመት ውስጥ ያሉ 60 ወንዶችና 49 ሴቶች ናቸው፤ በዜግነትም ሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸውም 81 ከአዲስ አበባ፣ ዘጠኝ ከኦሮሚያ፣ አራት ከሶማሌ፣ አራት ከደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ ሦስት ከአማራ፣ ሦስት ከትግራይ፣ ሦስት ከአፋር እና ሁለት ከሀረሪ ክልል ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 118 ሰዎች አገግመዋል፤ አጠቃላይ ያገገሙትም 738 ደርሰዋል፡፡

በ24 ሰዓታት ውስጥ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በሀገሪቱ እስከ ዛሬ በቫይረሱ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች 61 ደርሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን ለ192 ሺህ 87 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተካሂዶ በ3 ሺህ 630 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

Previous articleከገጠር እስከ ከተማ ተስፋ የተሰነቀበት የሥራ መስክ ተስፋ ሰጪ ሆኗል፡፡
Next articleበአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ሦስት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፡፡