
አዲስ አበባ: ኅዳር 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ ሁሴን አልዬ (ዶ.ር) ባለፉት አራት ዓመታት በተሠሩ የሌማት ትሩፋት ሥራዎች የእንስሳት ሃብት ላይ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
በተለይም በወተት መንደር ምስረታ፣ በንብ ማነብ፣ በዶሮ እና እንቁላል ምርት እንደዞን አመርቂ ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል። በዞኑ 214 የወተት መንደር ለመገንባት ታቅዶ 228 መንደሮችን ማቋቋም ተችሏል ብለዋል።
አርሶ አደሮች በወተት ምርት ተጠቃሚ እንዲኾኑ የገበያ ትስስር ሥራ እየተሠራ መኾኑንም አክለዋል። ዞኑ በወተት ምርት ሰፊ አቅም ያለው በመኾኑ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ የተቀነባበሩ የወተት ምርቶችን ለማስቀረት እየተሠራ መኾኑንም ጠቁመዋል።
ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
