“የአብሮነት ተምሳሌት፣ የታሪክ እና የጥበብ አምባዋ ደሴ ከተማ ገብተናል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

3

ባሕር ዳር: ኅዳር 5/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ የክልል እና የፌደራል የመንግሥት ሥራ ኀላፊዎች ደሴ ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት “የአብሮነት ተምሳሌት፣ የታሪክ እና የጥበብ አምባዋ ደሴ ከተማ ገብተናል” ብለዋል።

በወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን ለደሴ ከተማ ከንቲባ፣ ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለከተማው ሕዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ነው ያሉት፡፡

በቆይታቸው በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን የሥራ ሂደት የምንመለከት ይኾናል ብለዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኅብረብሔራዊ አንድነትን በማጎልበት ኢትዮጵያን ማበልጸግ ይገባል።
Next articleመተጋገዝ እና መተባበር ለሲቪክ ማኅበራት ቀጣይነት ሚናው የጎላ ነው።