
ወልድያ: ኅዳር 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል በሰሜን ወሎ ዞን እና በወልድያ ከተማ አሥተዳደር “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ መልዕክት በፓናል ውይይት ተከብሯል።
በመድረኩ የሰሜን ወሎ ዞን ፍትሕ መምሪያ ኀላፊ ፍስሀ መንግሥቴ የፍትሕ ሥርዓቱ ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለመፍጠር ሚና እንዳለው አስረድተዋል።
በተለይም በሕገመንግሥቱ የተቀመጡ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት የሚያጎለብቱ መብቶች እንዳይጣሱ በማድረግ እና ለኢትዮጵያውያን እኩል ፍትሕ በማስፈን አብሮነትን የማስቀጠል ሚና እንዳለው ነው ያሳሰቡት።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር አፈ ጉባኤ ኢቶጲስ አያሌው “ለኢትዮጵያ ምን ሠራንላት ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን” ብለዋል።
የሀገር አደራ እና ውለታ በተግባር ሊገለጽ ይገባል ያሉት አፈጉባኤው ኅብረብሔራዊ አንድነትን በማጎልበት የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ ይገባልም ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
