የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ሰላም፣ አንድነት እና ፍቅር የሚሰበክበት የኢትዮጵያውያን ቀን ነው።

6
ደባርቅ: ኅዳር 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ መልዕክት በደባርቅ ከተማ ተከብሯል።
ልዩነትን በማቻቻል እና አንድ በሚያደርጉ የጋራ ጉዳዮች በመምከር ሀገራዊ ዕድገትን ማፋጠን እንደሚገባ የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት ገልጿል።
የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ዳኛው አበራ ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መገኛ ሀገር መኾኗን ገልጸዋል። ኅብረ ብሔራዊ አንድነቷን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
ልዩነት ውበት እንጂ የጠብ እና የክርክር ምክንያት ሊኾን አይገባም ያሉት አቶ ዳኛው የመከባበር እና የመፈቃቀር ነባር ሀገራዊ እሴቶችን ማስቀጠል ይገባል ነው ያሉት።
የበዓሉ አስተባባሪ እና የደባርቅ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኀላፊ ጀማል ሲሳይ ተማሪዎች በበዓሉ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በዓሉ ልጆች ስለሀገራቸው እንዲያውቁ እና ግንዛቤያቸውን እንዲያሰፉ እንደሚያግዛቸውም አስረድተዋል።
የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ሰላም፣ አንድነት እና ፍቅር የሚሰበክበት የኢትዮጵያውያን ቀን ነው ብለዋል።
ተሳታፊ ተማሪዎችም በመርሐ ግብሩ መሳተፋቸው ስለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ያላቸውን አመለካከት እና ግንዛቤ እንዲያዳብሩ እንዳገዛቸው ገልጸዋል።
የመከባበር እና የመተሳሰብ ሀገራዊ እሴትን ማስቀጠል እንደሚገባም ተናግረዋል።
በመርሐ ግብሩ ሲሳተፉ አሚኮ ያነጋገራቸው ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ስለአንድነት የሚሰበክበት የአብሮነት በዓል ነው ብለዋል።
ልዩነትን በማቻቻል እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ሀገራዊ ዕድገትን ማረጋገጥ እንደሚገባም ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ኢትዮጵያ ምድሯ ባለ ሦስት ድርብ ሃብት የያዘ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleምርት እንዳይባክን በጥንቃቄ መሠብሠብ ያስፈልጋል።