የብሔር ብሔረሰቦችን በዓል ለማክበር ወደ አካባቢው የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት ተደርጓል፡፡

5
አዲስ አበባ: ኅዳር 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀንን ለማክበር ወደ ሆሳዕና የሚጓዙ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ አስታውቋል።
ልዩ ወረዳው ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኅን ለተውጣጡ ባለሙያዎች በቆሼ ከተማ አቀባበል አድርጓል።
የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ጀማል አማሮ ወረዳው በተለያዩ የተፈጥሮ ሃብቶች የታደለ እና በፈጣን የልማት ግስጋሴ ላይ ያለ መኾኑን ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በአካባቢው አልፎ አልፎ ያጋጥሙ የነበሩ የጸጥታ ችግሮች ተቀርፈው ልዩ ወረዳው በሰላም እና መረጋጋት ውስጥ መኾኑንም ጠቁመዋል።
በተለይም 20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን ለማክበር ወደ ሆሳዕና የሚያልፉ ተጓዦች ወረዳውን አልፈው የሚሄዱ በመኾኑ አስፈላጊውን አቀባበል ለማድረግ፣ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት፣ የተረጋጋ ሰላም እና የባሕል እሴትን ለማሳየት ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።
የማረቆ ልዩ ወረዳ በተለየ ሁኔታ በበርበሬ ምርቱ እንደሚታወቅም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ለኅብረ ብሔራዊነት ግንባታ አስፈላጊ ነው።
Next article“ኢትዮጵያ ምድሯ ባለ ሦስት ድርብ ሃብት የያዘ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ