የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበር ሀገራዊ እሴቶች እንዲጠበቁ ያስችላል።

2

እንጅባራ: ኅዳር 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት “በሚል መሪ መልዕክት በእንጅባራ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሙሉዓዳም እጅጉ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበር ሀገራዊ እሴቶች እንዲጠበቁ እና በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ማኅበራዊ መስተጋብር እንዲጠናከር የጎላ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

ባለፉት 19 ተከታታይ ዓመታት በተከበሩ በዓላት የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች ባሕላቸውን፣ ወጋቸውን እና ማንነታቸውን እንዲጠብቁ እና ለተቀሪው ዓለም እንዲያስተዋውቁ ዕድል ፈጥሯልም ነው ያሉት።

በታሪክ የተዛባውን የብሔር ብሔረሰቦች ግንኙነት በማረቅ ለሀገር አንድነት እና ሰላም በጋራ መቆም እንደሚገባም አፈ ጉባኤዋ አስገንዝበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም የፌዴራሊዝም ሥርዓት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ባሕላቸውን እንዲያለሙ፣ እርሰ በእርስ እንዲተዋወቁ እና ጉልተው በመውጣት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ድምቀት እንዲኾኑ ያስቻለ መኾኑን ተናግረዋል።

ብዝኅ ሃይማኖት፣ ብኀኅ ባሕል እና ብዝኅ ቋንቋ ባለቤት በኾነች ሀገር ውስጥ ተከባብሮ እና ተባብሮ ለሀገራዊ አንድነት ከመቆም ውጭ አማራጭ እንደሌለም ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።

በመድረኩ ዴሞክራሲ እና የፌዴራሊዝም ሥርዓት ተስፋዎች እና ተግዳሮቶች በሚል ርዕስ መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“መፍጠር፣ መፍጠን እና በጥራት መሥራት የሁልጊዜም የሥራ መመሪያችን ሊኾን ይገባል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleስለሪህ በሽታ ምን እንወቅ?