
ባሕር ዳር: ኅዳር 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ በጫካ ሲንቀሰቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው።
በወረኢሉ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በእነርሱ አደረጃጀት የሻለቃ አዛዥ የነበረ ቃሉ አስፋው፣ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የነበረ ሡልጣን ሲሳይ እና ሌሎች ታጣቂዎች ናቸው የሰላም አማራጭን የተቀበሉት።
ከደቡብ ወሎ ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ታጣቂዎቹ ስናይፐርን ጨምሮ ሌሎች ትጥቆችን በመያዝ ነው የሰላም አማራጭን የተቀበሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
