የሦስትዮሽ ድርድሩ ዛሬ በኢትዮጵያ መሪነት እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ አስታወቀ፡፡

216

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 09/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኢፌዴሪ ውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሕዳሴ ግድቡ ጉዳይ ለ5ኛ ቀናት የተካሄደውን የሦስትዮሽ ድርድር አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡

የ5ኛ ቀን ድርድሩ በግብጽ መሪነት መካሄዱን፣ ሦስቱም ሀገራት በሕዳሴ ግድቡ የመጀመሪያ ዙር ውኃ አሞላል እና የግድቡ ዓመታዊ የውኃ አጠቃቀም ላይ ትኩረት አድርገው መወያዬታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ሀገራቱ ከዚህ ድርድር በፊት በነበሩት ቀናት የመጀመሪያ ዙር የግድቡ የውኃ አሞላል መርሆዎች፣ የአካባቢያዊ እና ማኅበራዊ ተጽዕኖዎች ጥናቶች፣ መርሆዎችን እና ህግጋትን ወደ ተግባር ማስገባት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መደራደራቸውንም በግለጫው አስታውሷል፡፡

ድርድሩ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 9/2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሪነት እንደሚቀጥልም የኢፌዴሪ ውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleየደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጋላጭ ከሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ናሙና እየወሰደ ነው።
Next articleየኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ከተረጋገጡ 16 አሽከርካሪዎች መካከል ስድስቱ መገኘታቸውን ጤና መምሪያው አስታወቀ፡፡