
ወልድያ: ኅዳር 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን በራያ ቆቦ ወረዳ አራዱም ቀበሌ አስጀምሯል።
የዘር ማስጀመሪያ ማሳ ላይ አሚኮ ያገኛቸው አርሶ አደሮች ከአሁን በፊትም በበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ምርት በማግኘት ተጠቃሚ መኾናቸውን ተናግረዋል። አሁን በሚዘሩበት ማሳም ምርታማ እንደሚኾኑ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
ቀድመው በኩታገጠም በማሳረስ እና በቂ ግብዓት በማሟላት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን አንስተዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ ተገኝ አባት በዞኑ በበጋ መስኖ ልማት እና በበልግ ዝናብ 26 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ እንደሚለማ ተናግረዋል።
ከዚህ ውስጥ 14 ሺህ 500 ሄክታር መሬት በመስኖ የሚለማ መኾኑን ለአሚኮ ገልጸዋል። የምርጥ ዘር እና የማዳበሪያ ግብዓት በበቂ ሁኔታ ቀርቧል ነው ያሉት።
እስከ ምርት ሥብሠባም የባለሙያ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
