10ኛው የከተሞች ፎረም የቅድመ ዝግጁት ሥራ መጠናቀቁን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትቴር አስታወቀ።

3
አዲስ አበባ: ኅዳር 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 10ኛው የከተሞች ፎረም ከኅዳር ስድስት እስከ 10/2018 ዓ.ም ድረስ በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ ይካሄዳል።
ፎረሙን አስመልክቶ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል።
በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ ለሚካሄደው የከተሞች ፎረም ዝግጁቱ መጠናቀቁን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ገልጸዋል።
በ10ኛው የከተሞች ፎረም ተሳታፊ ከተሞች ልምድ ይለዋወጡበታል ብለዋል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም በፎረሙ በከተማ ልማት ዙሪያ ያካሄዱትን ጥናት ያቀርባሉ ነው ያሉት። ጥናቱ ለፖሊሲ አውጭዎች ግባት እንደሚኾንም አንስተዋል።
“በሀገር አቀፍ ደረጃ 73 ከተሞች የኮሪደር ልማትን እየተገበሩ ይገኛሉ” ነው ያሉት። በከተሞች ፎረም የኮሪደር ልማትን የተገበሩ ከተሞች ልምዳቸውን ያካፍላሉም ተብሏል።
ዘጋቢ:- ተመስገን ዳረጎት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየኢትዮጵያ የጸረ ድህነት ትግል እና የግብጽ ሴራ
Next articleየብሔር ብሔረሰቦች ቀን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የሚጠናከርበት ነው።