
አዲስ አበባ: ኅዳር 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚኒስቴር የዲጂታል ጤና ኤግዚቪሽን እያካሄደ ነው።
በኤግዚቪሽኑ ጤንነቴ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያም ይፋ ኾኗል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ጤንነቴ የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ የጤና አገልግሎትን የሚያፋጥን ከመኾኑ ባሻገር የመድኃኒት አሥተዳደር ሥርዓትን በማዘመን የመድኃኒት ሥርጭት እና አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ተናግረዋል።
በጤና ሚኒስቴር ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ የዲጂታል አገልግሎቶች መከላከል ላይ የተመሠረተውን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ እና የዲጂታል ሕክምና አገልግሎትን ለማቀላጠፍ የሚያስችሉ መኾናቸውንም ገልጸዋል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ተቋሙ እየሠራቸው ያሉ ተግባራት የ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂን በጤናው ዘርፍ ለማሳካት የሚያስችሉ እመርታዎች መኾናቸውን ተናግረዋል።
በሀገር ውስጥ እና በራስ አቅም የተዘጋጀው መተግበሪያ የዜጎችን እንግልት በማስቀረት እና ጊዜን በመቆጠብ ለዘርፉ የአገልግሎት ጥራት የላቀ አበርክቶ ይኖረዋል ብለዋል።
ዘጋቢ:- ረህመት አደም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
