የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተጨባጭ ልማትን እንዳመጡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

5

አዲስ አበባ: ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ከፍተኛ መሪዎች በሁለተኛ ቀን ጉብኝት የአዲስ አበባ ከተማ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።

በየኮሪደር ልማት ተነሽ ለኾኑ ዜጎች በመልሶ ማቋቋም ዘመናዊ ቤቶች እንደተሠሩላቸውም ተብራርቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ከድር ጀማል በከተማው በአሁኑ ጊዜ በዓመት 47 ሺህ ቤቶች እየተገነቡ ይገኛሉ ብለዋል።

የኮሪደር ልማት የከተማዋን ችግሮች በአግባቡ ሊቀርፍ በሚችል መልኩ ዲዛይን ተደርጎ የተተገበረ እና እየተተገበረ የሚገኝ መኾኑን ተናግረዋል።

ሥራው በዋናነት የመሪነት ቁርጠኝነት፣ ፍጥነት፣ ፈጠራ፣ አካታችነት፣ ወጭ ቆጣቢነት እና በመረጃ ላይ የተመሠረተ ፈጣን ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ተመስርቶ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ኮሪደር ልማቱን መሠረት አድርጎ በግሉ ዘርፍ እና በተቋማት ትብብር የ1 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር ፕሮጀክት ከኮሪደር ልማት በተያያዘ እየተሠራ ነው ብለዋል።

43ሺህ ካሬ ስኩየር ስፋት ባላት አዲስ አበባ በሥራው መድረስ የተቻለው 5ሺህ ሄክታር ብቻ መኾኑን አንስተዋል።

በዚህ የኮሪደር ልማት በ65 ሄክታር ላይ 135 የመኪና ማቆሚያ ስፍራ እና 285 ኪሎ ሜትር መንገድ መገንባቱም ተብራርቷል።

በዚህም ለኮሪደር ልማት ተነሺዎች 20 ቢሊዮን ብር ካሳ ተከፍሏል። 1ሺህ 300 ሄክታር መሬት ትክ ቦታ መሰጠቱንም ተናግረዋል።

በፒያሳ አካባቢ እየተገነባ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ፕላዛዎች፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት፣ የሕጻናት መዝናኛ ስፍራዎች እና ሌሎች የተገነቡ ዘመናዊ የመዝናኛ እና የንግድ አካባቢ መፈጠሩ ተነግሯል

በፊት በከፍተኛ ሁኔታ ቅሬታ ይነሳበት የነበረው የኮርሪደር ልማት አሁን በየአካባቢው እንዲደርስ በኅብረተሰቡ ተናፋቂ ኾኗል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ በብልጽግና ፓርቲ ዕይታ ሁነትን እንዴት መቀየር እንደሚቻል በኮሪደር ልማቱ የታየበት እንደኾነም ተናግረዋል። መፍጠር እና መፍጠንን መሠረት ተደርጎ እየተሠራ እንደኾነም አስረድተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አተያይን በማስተካከል ከእሳቤ እስከ አመራር ትምህርት የሰጡበት ላይ መሠረት ተደርጎ የመጣ ለውጥ ነውም ብለዋል።

በቤት ልማት ላይ ያለውን ችግር ለመፍታት በግልም ኾነ በመንግሥት ትብብር ለመሥራት በማሰብ በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት ብቻ 100 ሺህ ቤት በመገንባት ሂደት ላይ እንደኾኑም ጠቁመዋል።

የከተማ ነዋሪውን በልማት ሥራ ላይ በማሳተፍ እና በመሸለም ውጤታማ የልማት ትብብር መፍጠር ተችሏል ነው ያሉት።

ከ47 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማት ስፍራ ውስጥ የተጎበኘው 5 ኪሎ ሜትር ብቻ መኾኑን ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የጎንደር አብያተ መንግሥታት የማንነታችን መገለጫ ናቸው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next article“ጥገናው የጎንደርን ትንሳዔ ከ400 ዓመታት በኋላ የሚያሳይ ነው” አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር