የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።

2

ባሕር ዳር: ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በምሥራቅ ሸዋ ዞን የቦራ ወረዳ ላይ እየተከናወነ ያለው የልማት ሥራ ከተጎበኙት መካከል ነው፡፡

በጉብኝቱ ላይ የታደሙት የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ.ር) ብዝኀ ኢኮኖሚ አካሄድን መከተል መጀመራችን ብልፅግናን ለማሳካት ትክክለኛው መንገድ ላይ መሆናችንን ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በብልፅግና ሂደት ውስጥ ገጠሩን ማሸጋገርና ማዘመን ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ኤርጎጌ አርሶ አደሩ ለፍጆታ ከማምረት በዘለለ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ሂደት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

በገጠር ትራንስፎርሜሽን ከማምረት ለውጪ ገበያ እስከማቅረብ የዘለቀ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ገጠሩን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ስለመመልከታቸው የተናገሩት ሚኒስትሯ ገጠሩንና ከተማውን ለማስተሳሰር የተሄደበት ርቀት በጎ ጅምሮች መኖራቸውን ያመላከተ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የጎንደር አብያተ መንግሥታት ጥገናን መርቀው ከፈቱ።