በኢትዮጵያ ተጨማሪ 176 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ ሦስት ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል፡፡

259

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 08/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 636 ሰዎች በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ በ176 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ከ5 እስከ 90 ዓመት ያሉ 116 ወንዶችና 60 ሴቶች ሲሆኑ 175 ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ አዲስ ቫይረሱ የተገኘባቸው 98 ሰዎች ከአዲስ አበባ እና 2 ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ናቸው፡፡ ከክልሎች ደግሞ አማራ 33፣ ትግራይ 31፣ ሶማሌ 7፣ ኦሮሚያ 3 እና አፋር 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ዛሬ አረጋግጠዋል፡፡

ሁለት በሕክምና ማዕከል የነበሩ ሰዎች ሕይወት ማለፉንም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፤ አንድ ሰው ደግሞ ሕይወቱ ካለፈ በኋላ በተደረገ ምርመራ ቫይረሱ እንዳለበት ተረጋግጧል፡፡ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥርም 60 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ዛሬ ሪፖርት ከተደረጉት ሞቶች ሁለቱ ከአማራ ክልል አንዱ ከአዲስ አበባ ናቸው፡፡

ትናንት በኢትዮጵያ 75 ሰዎች ማገገማቸውን ያስታወቀው የጤና ሚኒስቴር አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 620 መድረሱን አመልክቷል፡፡

በኢትዮጵ እስከዛሬ ለ186 ሺህ 985 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ በ3 ሺህ 521 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ተገኝቷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የ60 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ 2 ሺህ 839 ሰዎች ደግሞ በሕክምና ላይ ናቸው፤ 29 ሰዎች በጽኑ ሕሙማን ክፍል ይገኛሉ፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleበሰሜን ሸዋ ዞን 22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡
Next articleየደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጋላጭ ከሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ናሙና እየወሰደ ነው።