የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማነቃቃት በቅንጅት መሥራት ያስፈልጋል።

1
ገንዳ ውኃ: ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎንደር ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማነቃቃት መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልኾኑ አበዳሪ ተቋማት ጋር በገንዳ ውኃ ከተማ ውይይት አካሂዷል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ተወካይ እና የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ መሰንበት መልካሙ የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ዘርፉን በማነቃቃት ዞኑን የልማት መዳረሻ ለማድረግ በቅንጅት መሥራት ይገባል ብለዋል።
ሁሉንም የዞኑን ጸጋዎች ለአልሚ ባሃብቶች ለማስተዋወቅ ጥረት እየተደረገ መኾኑንም አንስተዋል። ምቹ የልማት ቦታዎችም ዝግጁ ኾነው እንደሚገኙ ነው የተናገሩት።
የባለሃብቶችን ችግር ከሚመለከተቻው አካላት ጋር በመኾን መፍትሔ በማበጀት የኢንዱስተሪውን ዘርፍ ለማጠናከር በተለየ መልኩ እየተሠራ መኾኑንም አብራርተዋል።
የምርት መሰብሰቢያ፣ ማበጠሪያ ማሽኖችን እና የብድር ሁኔታዎችን ለማመቻቸት በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።
የገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተወካይ ታድሎ አቡሃይ በከተማዋ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃት ከ133 ነጥብ 65 ሄክታር በላይ መሬት ተከልሎ የመሠረተ ልማት ሥራ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
በከተማው ከ14 በላይ የሚኾኑ ባለሃብቶች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልጸዋል።
በዚህ ዓመት በግንባታ ላይ ያሉ ባለሀብቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግም ጠቁመዋል።
በምዕራብ ጎንደር ዞን የዋሊያ ካፒታል ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ብርሃኑ ስመኘው በዞኑ ለአልሚ ባልሃብቶች የግብርና ግባቶችን፣ የሰሊጥ ማበጠሪያ እና ዘመናዊ የሰብል መውቂያ ማሽኖችን በማቅረብ ለባለሃብቶቹ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል።
ድርጅቱ በዞኑ የተሻለ ሥራ እንዲሠራ እና አካባቢው እንዲለማ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
በምዕራብ ጎንደር ዞን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዳ ውኃ ከተማ ቅርጫፍ ሥራ አሥኪያጅ ደመወዝ ምትኩ አካባቢው ለኢንቨስተመንት ዘርፉ ምቹ ሁኔታ ያለው በመኾኑ ያሉትን ጸጋዎች እና ሃብቶች አሟጦ በመጠቀም ማልማት ያስፈልጋል ብለዋል።
ቀጣይነት ያለው ልማትን ለማምጣት የኢንቨስትመንት ዘርፉን ማነቃቃት እና የጋራ ሥራዎችን መሥራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
ባንኩ ለአልሚ ባለሃብቶች የብድር ሁኔታዎችን እንደሚያመቻችም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleኢትዮጵያ ለፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ተቋማዊ እና መንፈሳዊ ሞዴል ሀገር ናት፡፡
Next articleሰሞነኛው ጉንፋን መሰል ሕመም ምንድን ነው ?