ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ የሕዝብ የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት እየተሠራ ነው።

3
ደባርቅ: ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዘላቂ ሰላም እና ልማትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠሩ እንደሚገኙ የዳባት ወረዳ እና የከተማ አሥተዳደሩ ገልጸዋል።
የዳባት ወረዳ አሥተዳዳሪ መርሻ ወረታ ከማኅበረሰቡ፣ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ከጸጥታ መዋቅር አባላት ጋር በመተባበር ሰላምን ለማጽናት የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን አብራርተዋል።
ከማኅበረሰቡ ጋር በመተባበርም የጋራ መግባባት የተፈጠረባቸው የሕዝብ መድረኮችን በማካሄድ የሕዝብ ግንኙነት ሥራውን ማጠናከር ተችሏል ብለዋል።
በዚህም ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሃይማኖት አባቶች ጋር በመተባበር በርካታ ቁጥር ያላቸው የታጣቁ አካላት በምህረት እንዲገቡ እና የበደሉትን ማኅበረሰብ በበጎ ምግባር እንዲክሱ የማድረግ ሥራ መሠራቱንም ገልጸዋል።
የዳባት ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሃብትሼት ሞገስ በበኩላቸው ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ሢሠሩ መቆየታቸውን አብራርተዋል።
ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በመጠጥ ውኃ፣ በመንገድ እና በሌሎች መሠረታዊ የልማት አውታሮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት መደረጉንም አስገንዝበዋል።
የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ተናበው በቁርጠኝነት መሥራት በመቻላቸው ዘርፈ ብዙ ለውጦች መገኘታቸውንም ገልጸዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የጸጥታ መዋቅር አባላት የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መኾኑን ጠቁመው ምሥጋና አቅርበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article44 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ ስንዴ ለማልማት ማቀዱን የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።