በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት 33 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው።

446

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 624 የላቦራቶሪ ምርመራ በ33 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡ ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ የተረጋገጡትም ስምንት ከምዕራብ ጎንደር ለይቶ ማቆያ፣ ሁለት ከምቦልቻ ከተማ አስተዳደር፣ አንድ ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ 22 ከሰሜን ሸዋ (16 ደብረብርን ከተማ፣ አራት ከእንሳሮ ወረዳ ልይቶ ማቆያ፣ አንድ ጣርማ በር ከጤና ተቋም ውስጥ ምርመራ ተደርጎለት ቫይረሱ የተገኘበት፣ አንድ ከሞጃና ወደራ (ሕይወቱ አልፎ በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ እንዳለበት የተረጋገጠ) ናቸው፡፡

በምርመራ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጡት ከ19 እስከ 80 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 31 ወንዶች እና ሁለት ሴቶች ናቸው።

በአማራ ክልል እስከ ዛሬ ሰኔ 8/2012 ዓ.ም ድረስ ለ5 ሺህ 590 ሰዎች የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ231 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡ በ24 ሰዓታት ውስጥ አምስት ሰዎች ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ሕክምና መስጫ ማዕከል አገግመዋል፡፡ በዚህም በክልሉ አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 44 ደርሷል፡፡

አንድ ሰው ከቦሩ ሜዳ ለይቶ ሕክምና ማስጫ ማዕከል በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወቱ አልፏል፡፡

በክልሉ በጽኑ ሕሙማን የሕክምና ክፍል ውስጥ የገባ ታማሚ አለመኖሩን እና ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ሕክምና መስጫ ማዕከል የሚገኙት ሁሉም ሰዎች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ቢሮው አስታውቋል።

Previous article“እንደ ናይል የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት በበላይነት ተቆጣጥረው የሚጠቀሙበት ወንዝ በዓለም የለም።” ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ
Next articleበሰሜን ሸዋ ዞን 22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡