የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ሕክምና መስጠት ጀመረ።

6
ደሴ: ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ከኪዩር ብላይንድነስ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ከጥቅምት 24 እስከ 29/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ነጻ የዐይን ሞራ ግዶሽ ቀዶ ጥገና ሕክምና መስጠት ጀምሯል።
ባለፉት ቀናት በተለያዩ ወረዳዎች የልየታ መርሐ ግብር ሲከናወን የቆየ ሲኾን የዐይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች በሆስፒታሉ ተገኝተው ሕክምና እየተደረገላቸው ነው።
አሚኮ ያነጋገራቸው ታካሚዎች ዐይናቸው ለረጅም ጊዜ ማየት አለመቻሉን ተከትሎ ለእንግልት ሲዳረጉ እንደነበር አስንተዋል። በተደረገላቸው ህክምና የዐይን ብርሃናቸው በመመለሱ ደስታቸውንም ገልጸዋል።
በቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል የዐይን ሕክምና ክፍል ኀላፊ እንዳልክ ያረጋል የዐይን ሞራ ግርዶሽ ሲከሰት በጤና እና በማኅበራዊ ሕይዎት ላይ ጉዳቱ ከፍ ያለ ነው ብለዋል።
የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ አሥኪያጅ ሲሳይ ተበጀ ሆስፒታሉ ከኪዩር ብላይንድነስ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ከ2 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ታካሚዎች ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ሕክምና እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
በቀጣይ ሆስፒታሉ ለታካሚዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማዘመን እና ለበርካታ ሕሙማን ሕክምና ለመስጠት ከአጋር አካላት ጋር ለመሥራት ዕቅድ መያዙንም አቶ ሲሳይ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ:- ሰልሀዲን ሰይድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየውስጥ ባንዳዎችን አምርሮ መታገል ይገባል።