
ደሴ: ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ አሥተዳደር “የውስጥ እና የውጭ ባንዳዎችን በማምከን አንፀባራቂ ድሎችን እናስመዘግባለን” በሚል መሪ መልዕክት የሰላም የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
የፀጥታ አባሉ የውስጥ ባንዳነትን በመታገል የተጀመሩ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት የተናገሩት የደሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሰይድ ካሳው ናቸው።
የመድረኩ ዓላማ ሰላምን የማፅናት ነው ያሉት አቶ ሰይድ የከተማችን የፀጥታ አካላት ለከተማዋ ብሎም ለቀጣናው ያበረከቱት መልካም አስተዋፅኦ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት የደሴ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ምክትል ኀላፊ አወል አሕመድ ከለውጡ በኋላ በርካታ የፖለቲካ ድሎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። ጉዞው ፈተናዎች የበዙበት እንደነበርም ተናግረዋል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ሰይድ አሊ እንደገለጹት በከተማው ብሎም በቀጣናው ሰላምን ለማፅናት እና የውስጥ ባንዳዎችን አምርሮ በቁርጠኝነት መታገል እንደሚገባ አንስተዋል።
የከተማው የፀጥታ ኀይል በቂ ዝግጅት አለው ብለዋል። ሰላምን ለማፅናትም የውስጥ ባንዳዎችን አምርሮ በቁርጠኝነት መታገል እንደሚገባ አንስተዋል። ለዚህም የከተማው የፀጥታ ኀይል በቂ ዝግጅት አለው ብለዋል።
ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት እንዳብራሩት የከተማችን ብሎም የቀጣናውን ሰላም ለማፅናት እስከ መስዋዕትነት ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መኾናቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ደምስ አረጋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
            
		