
ባሕር ዳር: ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን በፎገራ ወረዳ በዓለምበር እና ወጅ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የሰላም አማራጭን ለተቀበሉ ታጣቂዎች የደቡብ ጎንደር ዞን የሥራ ኀላፊዎች እና የጸጥታ ተቋማት መሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉት በጌታሁን ሙጬ ይመሩ የነበሩ 12 ታጣቂዎች ናቸው። ታጣቂዎቹ ሁለት ብሬን፣ አንድ የቃታ መሳሪያ እና ሰባት ክላሽ በመያዝ ነው የሰላም አማራጭን የተቀበሉት።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጎን ተሰልፈን ሕዝባችን አንወጋም ብለዋል።
ከደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የውጭ ባዕዳና የውስጥ ባንዳዎች ተላላኪ ልንኾን አንችልም፤ በቀጣይ የበደልነውን ሕዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
            
		