አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ጠቅላላ ሃብቱን 54 ቢሊዮን ብር አደረሰ።

4

አዲስ አበባ: ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ 21ኛ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዓለም አስፋው
አንበሳ ባንክ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ከ340 በላይ ቅርንጫፎች፣ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ደንበኞች እና ከ6 ሺህ 800 በላይ ሠራተኞች እንዳሉት ገልጸዋል።

ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት ከ36 ቢሊዮን በላይ ብር ብድር ማቅረቡን እና 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ማስመዝገቡንም ተናግረዋል። 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን እና ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘቡን 54 ቢሊዮን ብር ማድረሱንም ገልጸዋል።

ማኅበራዊ ኀላፊነቱን በመወጣት ረገድ ለቀጥታ ድጋፍ 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር፣ ለሲቢክ ማኅበራት ደግሞ
5 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መስጠቱንም የቦርድ ሰብሳቢው አንስተዋል።

ዘመኑን የዋጁ የቴክኖሎጂ አሠራሮችንም በመከተል ተደራሽነቱን ለማስፋት ባንኩ ሠርቷል ብለዋል። ለዚህም “አለኝታ” የተባለን መተግበሪያ በመጠቀም ዲጅታል አሠራርን ተግብሯል ሲሉ ገልጸዋል። “አልነጃሺ” የተባለ ከወለድ ነጻ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝም ተነስቷል።

በቀጣይ ዓመት ባንኩ የሰው ኃይል ላይ፣ ካፒታልን ማሳደግ ላይ እና ዲጅታላይዝድ አሠራርን ማስፋት ላይ የትኩረት አቅጣጫዎቹ እንደኾኑ በጉባኤው ተገልጿል።

በጉባኤው አዳዲስ የቦርድ አባላትን መምረጥ ጨምሮ ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ቀርበው ጸድቀዋል።

ዘጋቢ:- አዲሱ ዳዊት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተፋሰስ ልማት ሥራው ምርታማነት በመጨመር ተጨባጭ ለውጦችን አምጥቷል።
Next articleአንድነት የችግሮች መፍቻ እና የዘመናዊ ሀገር ግንባታ መሠረት ነው።