የተፋሰስ ልማት ሥራው ምርታማነት በመጨመር ተጨባጭ ለውጦችን አምጥቷል።

7

እንጅባራ: ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በ2018 የበጋ ወራት 506 ነባር እና አዳዲስ ተፋሰሶችን ለማልማት ታቅዷል።

በተፋሰስ ልማት ሥራው ከ228 ሺህ በላይ አልሚ የሰው ኀይል ይሳተፋልም ነው የተባለው።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ የተፋሰስ ሥራውን ለማሻሻል የሚያስችል ባለ ድርሻ አካላት የተሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ በእንጅባራ ከተማ አካሂዷል።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኀላፊ ቤዛዊት ጌታሁን የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ ኅብረተሰቡን ከተፈጥሮ ጋር ይበልጥ እያቆራኘ መምጣቱን ተናግረዋል።

በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ለረጅም ዓመታት የተተገበረው የተፋሰስ ልማት ሥራ የአካባቢ ገጽታን በማሻሻል እና በሰብል ምርታማነት ተጨባጭ ለውጦችን ማስመዝገቡንም ገልጸዋል።

ወጣቶች በለሙ ተፋሰሶች በከብት ማድለብ፣ በንብ ማነብ እና በአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት በማሰማራት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እያረጋገጡ እንደኾነም አንስተዋል።

በዘንድሮው የበጋ ወራትም ካለፉት ዓመታት ልምድ በመነሳት 506 አዳዲስ ተፋሰሶችን ለማልማት እና ነባር ተፋሰሶችን ለማጠናከር ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።

የተፋሰሶች እና የአልሚ የሰው ኀይል ልየታ፣ የቅየሳ እና ሌሎችም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደኾነም ገልጸዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም የዚህ ዓመት የተፋሰስ ልማት ሥራ ችግር ፍቺ በኾነ መንገድ በጥራት እንዲፈፀም ዝግጅት እያደረጉ መኾኑንም ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመደበኛ እና የአድማ መከላከል ፖሊስ አባላት በደብረ ብርሃን ከተማ አቀባበል ተደረገላቸው።
Next articleአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ጠቅላላ ሃብቱን 54 ቢሊዮን ብር አደረሰ።