ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው።

5

ባሕር ዳር: ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የተሰጠውን ትኩረት አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፏል።

በመልዕክቱም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው ብሏል።

መንግሥት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት እንዲቻል የተኪ ምርት ስትራቴጂን በመቅረጽ ወደ ሥራ በመግባቱ ከፍተኛ ውጤቶች ተመዝገበዋል ነው ያለው።

ስትራቴጂው የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር፣ የወጪ ገቢ ምርት እንዲመጣጠን እና ሀገራዊ ሉዓላዊነትን እንዲረጋገጥ እያደረገ ይገኛል።

በተለይ በውስጥ አቅም መቅረብ የሚችሉ ዋና ዋና የገቢ ምርቶች ተለይተው ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርቶች እንዲተኩ ተኩረት መደረጉ የውጪ ምንዛሬ ከማዳን እና ከሥራ እድል ፈጠራ አንጻር ፋብሪካዎችን ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲኾኑ አድርጓል ብሏል።

የተኪ ምርት ስትራቴጂ በሁሉም ዘርፍ በተሟላ መልኩ ገቢራዊ መደረጉ ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፉ የተሻለ የሥራ ዕድል አጋጣሚ መፍጠሩንም አመላክቷል።

ባለፉት ሦሥት ወራት ብቻ በተለያዩ ዘርፎች በተኪ ምርት ላይ በተከናወኑ ሥራዎች 1 ነጥብ 08 ቢሊየን የአሜርካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማዳን ተችሏል።

በሀገራችን ነባራዊ የፍጆታ ፍላጎት አንፃር የትኞቹ ምርቶች በቅድሚያ ይተኩ በሚል በምግብ እና መጠጥ፣ በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ፣ በኪሚካልና ኮንስትራክሽን ፣ ብረታብረት ብረት እና ቴክኖሎጂ ላይ በማተኮር 96 ተወዳዳሪ ተኪ ምርቶች ተለይተው በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የተደረገው ጥረት እንደሀገር ፍሬ እያፈራ ይገኛል ።

ለአብነት የጥጥ ምርትን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን በአፋር ክልል አሚበራና ወረር ወረዳዎች በ2017/18 የምርት ዘመን በ110 ሺህ ሄክታር መሬት በጥሬ ጥጥ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ተገኝቷል። ዘንድሮው የምርት ዘመን ለኢንደስትሪዎች የሚፈለገውን ያህል የጥጥ ምርት በመጠንና በጥራት ማቅረብ ተችሏል ፡፡

የማኑፋክቸሪግ ኢንዱስትሪዎች የግብአት ችግር እንዳይግጥማቸው ሀገር ውስጥ ያለውን እምቅ አቅም ለመጠቀም በመንግሥት ሰፊ ሥራ እየተሠራ ነው።

ከመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በውጤቱም ተጨማሪ አሴት ያለውን የሀገር ውስጥ ምርት 60 በመቶ ለማድረስ እና የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበታዳጊ ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ‎እየተሠራ ነው።
Next articleዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የጸጥታ አካላቱ ከኅብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት እየሠሩ ነው።