የሂጂራ ባንክ እና የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት (መጅሊስ) በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።

16

አዲስ አበባ: ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሂጂራ ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተሰማርቶ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኝ ባንክ ነው።

ባንኩ ከተለያዩ አጋሮቹ ጋር በባንኪንግ እና በፋይናንስ ዘርፍ ልዩ ልዩ ስምምነቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል። ባንኩ የዚሁ አካል የኾነውን አብሮ የመሥራት ስምምነት ከኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት (መጅሊስ) ጋር ፈጽሟል።

ስምምነቱ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ሙስሊሞችን በተለይ ከወለድ ነጻ በኾኑ የባንክ ፋይናንስ (ብድር እና ቁጠባ) ለማገልገል በማሰብ የተካሄደ ነው።

የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት በሂጂራ ባንክ በኩል የባንኩ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ዳዊት ቀኖ እና በኦሮሚያ መጅሊስ በኩል ደግሞ ፕሬዝደንቱ ሼህ ጋሊ ሙክታር ናቸው።

ዘጋቢ፦ ድልነሳ መንግሥቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleማኅበረሰባዊ አንድነትን በማጠናከር ዘላቂ ሰላም እና ልማትን ማረጋገጥ ይገባል።
Next articleእርስ በእርስ መጠፋፋት ማንንም አሸናፊ አያደርግም።