የ25 ዓመታት የአሻጋሪ እድገት እና ዘላቂ ልማት እቅድን ለማሳካት የፍትሕ ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው።

22
ደብረ ብርሃን፡ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደርና የሰሜን ሸዋ ዞን የፍትሕ ተቋማት መሪዎች እና ሠራተኞች በአማራ ክልል የ25 ዓመታት የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ ላይ ተወያይተዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ በኃይሉ ገብረ ሕይወት የክልሉን የ25 ዓመታት የአሻጋሪ እድገት እና ዘላቂ ልማት እቅድ ለማሳካት የፍትሕ ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በየደረጃው የሚገኙ የፍትሕ ተቋማት ፈፃሚዎች የሚጠቅባቸውን ኀላፊነት ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት።
የደብረ ብርሃን ከተማ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተመስገን ዘገየ የፍትሕ ተቋማት ዘመናዊ አሠራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ለእቅዱ መሳካት በቁርጠኝነት ሊሠሩ ይገባል ብለዋል።
የክልሉን የ25 ዓመታት የአሻጋሪ እድገት እና ዘላቂ ልማት እቅድ ለማሣካት በየዓመቱ ከመሪ እቅዱ የተቀዳ እቅድ በማቀድ መሥራት ይገባል ያሉት ደግሞ የሰሜን ሸዋ ዞን ፍትሕ መምሪያ ኀላፊ ደመረ ቸሬ ናቸው።
የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ለእቅዱ መሳካት የፍትሕ ተቋማት ሠራተኞችና መሪዎች በቁጠኝነት ሊሠሩ እንደሚገባም በመድረኩ ተመላክቷል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች እቅዱ ክልሉን ካጋጠመው ቀውስ የሚያስወጣና የሚያሻግር ነው፤ እኛም ፍትሕን በማስፈን ለእቅዱ መሳካት የበኩላችንን ኀላፊነት እንወጣለን ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ሥነ ጊዮርጊስ ከበደ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየከፋ ኦዲት ግኝት ያለባቸው ተቋማት በፍጥነት እርምት መውሰድ አለባቸው።
Next articleየቅጥር ማስታወቂያ