
ባሕር ዳር: ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር “ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት የከፍተኛ እና የመካከለኛ ንግዱ ማኅበረሰብ ሚና” በሚል መሪ መልዕክት ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኀላፊ ኃይለ ማርያም እሸቴ መድረኩ የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ የሚመከርበት ነው ብለዋል።
ሰላም ከሌለ የንግድ ሥራ መሥራትም አስቸጋሪ በመኾኑ የንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ስለ ሰላም መመካከር ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የንግዱ ማኅበረሰብ ሰላሙን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን አላስፈላጊ የዋጋ ንረትን መቆጣጠር ላይ ከመንግሥት ጎን ኾነው እንዲያግዙም ጠይቀዋል።
በአቋራጭ እና በአጭር ጊዜ ለማደግ በማኅበረሰቡ ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የኑሮ ውድነቱን ማባባስ እንደኾነ ነው የገለጹት። “ግብረ ገብ ያልኾኑ ነጋዴዎችን ማጋለጥ ይገባልም” ብለዋል።
የአካባቢን ሰላም በማስጠበቅ በኩል የንግዱ ማኅበረሰብም የበኩሉን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፦ ፍሬሕይወት አዘዘው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
        👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
 
             
  
		