የብልጽግና ፓርቲ ዓመታዊ ሥልጠናውን ማካሄድ ጀመረ።

5

ባሕር ዳር: ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ የ2018 ዓመታዊ የከፍተኛ መሪዎች ሥልጠናውን ማካሄድ ጀምሯል።

ስልጠናው “በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ መልዕክት ለሚቀጥሉት 10 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

ሥልጠናው የመሪዎችን ዕውቀት፣ ክህሎት እና አቅም የሚገነቡ ልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች የሚቀርቡበት ነው ተብሏል።

በሥልጠናው ከ2 ሺህ በላይ ከፌዴራል እና ከክልል የተወጣጡ ከፍተኛ መሪዎች እንደሚሳተፉ ተመላክቷል።

ከብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው
ከሥልጠናው በተጓዳኝ የተግባር የመስክ የልማት ሥራ ጉብኝቶች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ምን እየተሠራ ነው ?
Next articleግብረ ገብነት የጎደላቸውን ነጋዴዎችን ማጋለጥ ይገባል።