“እውነተኛውን የሀገራችን ለውጥ የሚመራው የራሳችን ጽናት፣ ፈጠራ እና የሥራ ትጋት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

7

ባሕር ዳር: ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በምሥራቅ ሸዋ ዞን የነበረን ጉብኝት በክረምት የስንዴ ምርት ሥራዎች የተገኘውን ውጤት የምርት አሰባሰቡን በመመልከት ለመገምገም እና የበጋ ስንዴ ሥራ ማስጀመር ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል።

በዚያው አካባቢ የሙዝ፣ ፓፓያ እና አሳ ኩታገጠም ሥራዎችንም ተመልክተናል። ነባሩ ባሕላዊ የግብርና ዘዴ አሁንም ያለ ቢኾንም በሰፊው ለማረስ የሚያስችለው ሜካናይዜሽን እያደገ በመሄዱ የአካባቢውን የግብርና ብቁነት እና ምርታማነት እያሳደገ ይገኛል ነው ያሉት።

ወደኋላ መለስ ብለን የነበረውን አሠራር ስንገመግም እነዚህን መሰል ዘመናዊ ዘዴዎችን ከብዙ ዓመታት በፊት እንደ ሀገር ጀምረን ቢኾን ኖሮ የግብርና ምርታችን በከፍተኛ ደረጃ የተለየ ይኾን እንደነበር እንረዳለን። ዛሬ ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ የሚሄድ ምርታማነት እየተመለከትን እንገኛለን። ለማደግ ምንም አይነት የውጭ ድጋፍ አይመጣም። እውነተኛውን የሀገራችን ለውጥ የሚመራው የራሳችን ጽናት፣ ፈጠራ እና የሥራ ትጋት ነው ብለዋል በመልዕክታቸው ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመድኃኒት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት በትኩረት እየተሠራ ነው።
Next articleየትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ምን እየተሠራ ነው ?