የእንሰሳት ሃብትን በማዘመን ውጤት ለማምጣት እየተሠራ ነው።

7

ደብረ ማርቆስ: ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሠራ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን የእንሰሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት መምሪያ ገልጿል።

በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በሆርሞን እና በማዳቀል ሥራ ከ9ሺህ በላይ እንሰሳትን ዝርያ ማሻሻል እንደተቻለ የምሥራቅ ጎጃም ዞን እንሰሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት መምሪያ ኀላፊ ዳኘ ዋሴ ተናግረዋል።

በወተት፣ በማር፣ በእንቁላል እና ሥጋ ምርት የሚፈለገውን ምርት ለማግኜት እና የአርሶ አደሩን ሕይወት ለመለወጥ የሚያስችሉ ሥራዎች መሠራታቸውንም አብራርተዋል።

እንደ ሀገር የተጀመረውን የሌማት ትሩፋት ለማረጋጋጥ እና የሥርዓተ ምግብ ችግርን ለመቀነስ በእንስሳት ማድለብ፣ በዶሮ እንቁላል እና በወተት ዘርፍ ውጤታማ ሥራ መሠራቱን ኀላፊው ገልጸዋል።

በዞኑ በ10 ወረዳ እና ከተማ አሥተዳደሮች ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተሠራ እንደኾነም አስገንዝበዋል።

ከ30 በላይ ሸዶችን በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎች በመገንባት ወደ ሥራ እንዲገቡ እየተሠራ ነውም ብለዋል።

ወጣቶች ከአበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት ብድር እንዲያገኙ ድጋፍ እየተደረገ እንደኾነም ገልጸዋል።

በዘርፉ የወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ ወደ ሥራ እንዲገቡ እየተሠራ መኾኑም ከመምሪያው የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥርዓት ወደ ሥራ ገባ።
Next article“የታጠቁ ኃይሎች ከልብ ሰላም ሊፈጥሩልን ይገባል” የሃይማኖት አባቶች