ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥርዓት ወደ ሥራ ገባ።

6

አዲስ አበባ: ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራቾች እና ላኪዎች ማኅበር ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው።

የኮንፈረንሱ ዋና ዓላማ ትርጉም ያለው ውይይት ለመፍጠር፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ ንግድን ለማስተዋወቅ እና የግብርና ኤክስፖርት ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የሚያስችል ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው።

በተጨማሪም የዕፅዋትን፣ የእንስሳትን እና የሰውን ጤና የሚጠብቁ ውጤታማ የሳኒተሪ (sanitary) እና ፋይቶ ሳኒተሪ (phaytosanitary) ሥርዓቶችን ለመተግበር፣ አሕጉራዊ ብሎም ዓለም አቀፋዊ ትብብርን ለማሳደግ እና አቅምን ለማጎልበት ቁልፍ መድረክ ኾኖ እንዲያገለግል ታስቦ የተዘጋጀ መኾኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ገልጿል።

በኮንፈረንሱ የባለሥልጣኑ ዲጂታል ሥራዎች ሲተዋወቁ ዓለማቀፋዊ ኢፋይቶ(e-phayto)ም ተመርቋል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወንዳለ ሃብታሙ (ዶ.ር) እንዳሉት የኢፋይቶ(e-phayto) ሥርዓት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ጥራት ያላቸው መኾናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው።

ይህ መኾኑ ደግሞ በንግዱ የተሳሰሩ ሀገራትን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ያሳድጋል ብለዋል።

በሥርዓቱ 128 ሀገራት የተሳሰሩ ሲኾን ኢትዮጵያ ይህን ቴክኖሎጂ በማበልጸግ እና በማስተዋወቅ ግምባር ቀደም ኾና መገኘቷ በኮንፈረንሱ ተገልጿል።

ዘጋቢ፦ ረህመት አደም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለሀገር እና ለሕዝብ ሰላም ከአንድ ቤት የወጡ ወንድማማቾች
Next articleየእንሰሳት ሃብትን በማዘመን ውጤት ለማምጣት እየተሠራ ነው።