ለሰላም አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይገባል።

13
ባሕር ዳር: ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ”የውጭ ባዳዎችን እና የውስጥ ባንዳዎችን ቅዠት በማምከን አንጸባራቂ ድሎችን እናስመዘግባለን” በሚል መሪ መልዕክት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ውይይት እያካሄደ ነው።
በውይይቱ ወቅታዊ የክልሉ እና የኢትዮጵያ የሰላም እና የልማት ሥራዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ላይ የመወያያ ሃሳብ ቀርቧል።
አሚኮ በተገኘባቸው መድረኮች ከተሰጡት አስተያየቶች መካከልም የመሠረተ ልማት መስፋፋትን አድንቀው ለግል ጥቅም መሯሯጥ መብዛቱን አንስተዋል። ይህም ለሰላም እጦት እና ለመለያየት ምክንያት መኾኑን ገልጸዋል።
ጎጠኝነት በመስፋፋቱ፣ በአቋራጭ የመክበር ፍላጎት በመብዛቱ እና የሃይማኖት አባቶችም መክረው ባለማስተካከላቸው ችግሩ እንደተባባሰ ተነስቷል።
ተወያዮቹ የችግሩ ባለቤቶች እንደኾኑ ገልጸው መፍትሄውን መፈለግ እንዳለባቸውም ጠቁመዋል። ሁልጊዜ ልመና እና ጦርነት ሊሰለች እንደሚገባ እና ለሰላም አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸውም አስረድተዋል።
የኢትዮጵያን ብዝኀነት በመገንዘብ እና በመቀበል በአብሮነት መኖር መልመድ እንደሚገባም በአጽንኦት ገልጸዋል።
ጫካ የወጡ ወንድሞችንም መክሮ እና ገስጾ መመለስ እንደሚጠበቅም ተነስቷል።
የሃይማኖት አባቶች የንስሀ ልጆቻቸውን እና ተከታዮቻቸውን በማስተማር ቢመልሱ ለሰላሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነው የተባለው።
ያልተከፈቱ ትምህርት ቤቶች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባም ተጠቁሟል።
ዘጋቢ:- ዋሴ ባየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየፈተና ውጤት ማስታወቂያ
Next articleፖሊሳዊ ሥልጠናዎችን ወደ ተግባር በመተርጎም የሀገርን እና የሕዝብን ሰላም ማረጋገጥ ይገባል።