ማኅበረሰቡ አገልግሎት ለማግኘት እጅ መንሻ ከማቅረብ ይልቅ ለመብቱ መቆም አለበት።

2
ጎንደር: ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
ዘላቂ ሰላምን ለማስመዝገብ የመንግሥት ሠራተኞች ሚና ትልቅ በመኾኑ የተጀመሩ ሰላምን የማስፈን ተግባራትን እንደሚደግፉ ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።
በክልሉ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ሕዝቡን ለበርካታ ውስብስብ ችግሮች እንደዳረገው ተናግረዋል። ለሰላሙ መስፈን ሁሉም የመንግሥት ሠራተኞች ከራሳቸው በመጀመር የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን መቅረፍ እና አገልጋይነትን ተላብሰው መሥራት እንደሚያስፈልጋቸው ተነስቷል።
የውይይቱ መደረግ በልማት፣ መልካም አሥተዳደር እና በሰላም የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚያግዝ የገለጹት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር አካባቢ ጥበቃ፣ ጽዳት፣ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሆነዓለም አሻግሬ ናቸው።
የልማት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በማኅበረሰቡ ዘንድ ይነሳል ያሉት ኀላፊው ይህን ችግር ለመፍታት “ማኅበረሰቡ ከእጅ መንሻ ይልቅ ለመብቱ መቆም እንዳለበት” አሳስበዋል።
የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበረሰቡን በቀናነት ማገልገል እና የተጀመረውን ሰላም የማስፈን ሥራ መደገፍ እንደሚኖርባቸው የተናገሩት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኀላፊ ነጻነት መንግሥቴ ናቸው።
ዘጋቢ: ዳንኤል ወርቄ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleነጻ የሕግ ድጋፍ ምንድን ነው?
Next articleየመስኖ ፕሮጄክቶች ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው?