የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

6
አዲስ አበባ: ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ረሻድ ከማል ተቋሙ በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ኀላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን ገልጸዋል። የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉም የዚህ አካል ነው ብለዋል።
812 ደርዘን ደብተር እና 18ሺህ እስክርቢቶ ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ድጋፍ መደረጉንም ገልጸዋል።
የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለትውልድ ነገን የተሻለ ለማድረግ መሠረት እንደኾነም አስገንዝበዋል። በክልሉ ያለውን የግብዓት ችግር ለማቃለልም እንደተቋም መሰል ድጋፎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።
በክልሉ ትምህርት ቢሮ የኮታ ድልድል መሠረትም የተደረገው ድጋፍ ለደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምርያ ተሰጥቷል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ መቅደስ ብዙነህ በኮርፖሬሽኑ የተደረገው ድጋፍ በከተማ አሥተዳደሩ ያለውን የግብዓት ችግር በመቅረፍ ለትምህርት ጥራት የላቀ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
በዘርፉ በርካታ የግብዓት ችግሮች በመኖራቸው መሰል ድጋፎች ከባለሃብቶች፣ ከግብረሰናይ ድርጅቶች እና ከተቋማት ይጠበቃል ነው ያሉት።
የተደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ደጋፍ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነው። ከ800 በላይ ለሚኾኑ ተማሪዎች ተደራሽ እንደሚኾንም ተመላክቷል።
ዘጋቢ፦ አዲሱ ዳዊት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ማንም ፈለገም አልፈለግም ኢትዮጵያ ተዘግታ አትኖርም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleኢትዮጵያ የባሕር በር የሚያስፈልጋት ለቅንጦት ሳይኾን ከፍታን ለማረጋገጥ ነው።