“የኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት የቀጣናውን የኢኮኖሚ ውህደትና የጋራ ብልፅግናን በማፋጠን ለጋራ ከፍታ ምቹ መሠረት ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

11

ባሕር ዳር: ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ወንዞቿን ለቀጣናው የጋራ ብልፅግና የባህር በርን ደግሞ ለብሔራዊ ጥቅሟ የማረጋገጥ ፅኑ አቋም ይዛለች፡፡

ዛሬ ሁለተኛውን የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት በሳይንስ ሙዚየም ከፍተናል።

ኢትዮጵያ ለታዳሽ ኃይልና ለውሃ ልማት በሰጠችው ትኩረት በንጹህ ውሃና ኤሌክትሪክ አቅርቦት በርካታ ሚሊዮኖችን ተደራሽ በማድረግ ከፍተኛ መሻሻሎችን አምጥታለች።

ለቀጣናው የኢነርጂ ማዕከል በመሆንም ጎረቤቶቿን የታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ እያደረገች፣ ትስስርን እያጠናከረች፣ ለጋራ ብልፅግና እየተጋች ትገኛለች።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሀገራችን ለአካባቢው ላላት ብሩህ ራዕይ ብርሃን የፈነጠቀ፣ የአፍሪካ ብርሃን፣ የተፋሰሱ ሀገራትም የትብብር ዓርማ ነው።

የኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት የቀጣናውን የኢኮኖሚ ውህደትና የጋራ ብልፅግናን በማፋጠን ለጋራ ከፍታ ምቹ መሠረት ነው።

የውሃና ኢነርጂ ልማትን በዘላቂነት፣ በትብብር እና በፈጠራ መተግበር የጋራ እጣፈንታችን መሠረት መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleትምህርት ለትውልድ ግንባታ ያለውን ፋይዳ በመረዳት በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል።
Next article“ለሰላም መረጋገጥ ብቃት እና ቁርጠኝነት ያለው የጸጥታ ኃይል ያስፈልጋል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ