
አዲስ አበባ:ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 118ኛው የሠራዊት ቀን “የማትደፈር ሀገር፣ የማይበገር ሠራዊት” በሚል መሪ መልዕክት ተከብሯል።
በበዓሉ መልዕክት ያስተላለፉት የጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሠራዊቱ ለሀገር ሉዓላዊነት እና ነፃነት ሲል ጠላቶችን ድል እያደረገ ሀገር ማጽናቱን ገልጸዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ፣ የሀገሪቱ የጋዝ ማምረት መጀመር፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታን ጨምሮ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በግጭትም ውስጥ ተኹኖ የተሳኩ እና እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች መኾናቸውን አንስተዋል። ይህም የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያ እንደኾነ ጠቁመዋል።
ለኢትዮጵያ ሰላም እና ልማት የባሕር በር ወሳኝ ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኢትዮጵያን የባሕር በር የባለቤትነት ጥያቄ እናሳከዋለን ነው ያሉት።
በ118ኛው የሠራዊቱ ቀን በዓል ላይ በሙያቸው ለሀገራቸው ጥቅም ለሠሩ 34 ሲቪል ግለሰቦች ልዩ የመከላከያ ሠራዊት አባልነት የክብር የምስክር ወረቀት እና ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
