የሠራዊት ቀን አንድነታችን እንደማይናወጥ የምናሳይበት ነው።

5

አዲስ አበባ: ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 118ኛው የሠራዊት ቀን “የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት” በሚል መሪ መልዕክት በቢሾፍቱ ባሕር ኃይል ቅጥር ግቢ እየተከበረ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ የባሕር በር ጉዳይ ከሕጋዊነት፣ ታሪካዊነት እና ፓለቲካዊነት ባለፈ የሕልውና ጉዳይ መኾኑን ገልጸዋል።

በቀጣናው ያሉ ሀገራት በሰጥቶ መቀበል መርሕ በጋራ ለመሥራት መስማማት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። “ባሕር ኃይሉ የሀገሪቱን ጥቅም ለማስጠበቅ በሙሉ ቁመና ላይ ይገኛል” ብለዋል።

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ ሙሐመድ የሠራዊት ቀን አንድነታችን እንደማይናወጥ የምናሳይበት፤ የጀግናው መከላከያ ሠራዊትን ክብር ከፍ የምናደርግበት እና ለከፈለው የሕይወት መስዋዕትነት ምስጋና የምንቸርበት ነው ብለዋል።

ሠራዊቱ በየትውልዱ ጽኑ ጠባቂያችን መኾኑን በዘመናት አሳይቷል ያሉት ሚኒስትሯ እኛም 118ኛውን የሠራዊት ቀን ሲከበር ልባዊ ቃልን በማደስ መኾኑን ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ቤተልሔም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሀገራዊ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ሥራዎች ምቹ ከተማዎችን እየፈጠሩ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleየውል እርሻ ለምርት እና ምርታማነት ማደግ ድርሻው የጎላ ነው።