ወደ ትምህርት ገበታ ያልተመለሱ ተማሪዎችን ለመመለስ በትኩረት መሥራት ይገባል።

9

ጎንደር: ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከጎንደር ቀጣና የዞን እና የወረዳ የትምህርት ተቋማት የሥራ ኀላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማውን እያካሄደ ነው።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ደምስ እንድሪስ ባለፉት ዓመታት በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰላም እጦቱ ምክንያት የትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ችግር ገጥሞት ቆይቷል ብለዋል።

‎ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ የኾኑበት እና ትምህርት ቤቶች ተዘግተው የቆዩበት እንደነበር አንስተዋል።

ችግሩ አሁንም እንደቀጠለ መኾኑን የተናገሩት ምክትል ኀላፊው ‎ከ2 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች አሁንም እንደተዘጉ ይገኛሉ ብለዋል።

በ2018 ሩብ ዓመት የትምህርት ዘርፉ ላይ መነቃቃት እንዲፈጠር የተለያዩ ተግባራት እየተሠሩ መኾኑን አብራርተዋል። በሩብ ዓመቱ የነበረውን አፈጻጸም መነሻ በማድረግ ወደ ትምህርት ገበታ ያልተመለሱ ተማሪዎችን ለመመለስ በትኩረት መሥራት እንደሚጠበቅም ገልጸዋል።

‎የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው የትምህርት ሥርዓቱን ለማሳደግ የመምህራንን ብቃት እና ክብር መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል። ‎ ጥሩ ዜጋ ለመገንባት የትምህርት ዘርፉን ማዘመን ይጠበቃል ነው ያሉት።

‎ብቁ እና ንቁ የሰው ኀይል ለመፍጠር በትምህርት ዘርፉ ያሉ የሥራ ኀላፊዎች፣ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ተባብረው መሥራት እንደሚኖርባቸውም ገልጸዋል።

ዘጋቢ :- አዲስ አለማየሁ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!


Previous article“ነጻ ሃሳብ፣ ግልጽ ውይይት እና አሕጉራዊ የመፍትሔ አቅጣጫ የጣና ፎረም መለያዎች ናቸው” አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው
Next articleየኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እና ዓለመቀፍ የሥራ ድርጅት(ILO) የሥራ ስምሪት እና ፍልሰትን አስመልከቶ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።