“ነጻ ሃሳብ፣ ግልጽ ውይይት እና አሕጉራዊ የመፍትሔ አቅጣጫ የጣና ፎረም መለያዎች ናቸው” አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው

6

ባሕር ዳር:ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በየዓመቱ በአፍሪካ አሕጉር የሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ የሚመክረው ጣና ፎረም በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

“አፍሪካ በተለዋዋጭው የዓለም ሥርዓት ውስጥ” በሚል መሪ መልዕክት የተጀመረው 11ኛው የጣና ፎረም በአሕጉሪቷ የሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ ለቀጣዮቹ ሦስት ቀናት ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተለዋዋጭው ዓለም ውስጥ የአፍሪካ አቋም እና ቁመና ምን መምሰል እንዳለበት ሰፊ ውይይት ይደረጋል ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ናቸው።

ቃል አቀባዩ የፎረሙን ዓላማ አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ በ11ኛው የጣና ፎረም አፍሪካ አሕጉራዊ ጥቅሞቿን አስጠብቃ ለመዝለቅ የሚያስችል ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

“ነጻ ሃሳብ፣ ግልጽ ውይይት እና አሕጉራዊ የመፍትሔ አቅጣጫ የጣና ፎረም መለያዎች ናቸው” ያሉት ቃል አቀባዩ በፎረሙ አፍሪካዊ መፍትሔዎች እና የሰላም አማራጮች ይቀርባሉ ነው ያሉት።

አምባሳደር ነብያት በፎረሙ ከአሕጉሪቷ ፖሊሲ አውጭዎች፣ የፖለቲካ ልሂቃን፣ ምሁራን እና ተመራማሪዎች በተጨማሪ የአፍሪካ ጉዳይ ጉዳያቸው የኾኑ ተመራማሪዎችም ታድመዋል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጤናው ዘርፍ ስኬታማነት በታከሙ ታካሚዎች ብዛት ብቻ ሳይኾን እንዳይታመሙ በሚሠሩ አዳዲስ የጤና ሥራዎችም ነው የሚለካው።
Next articleወደ ትምህርት ገበታ ያልተመለሱ ተማሪዎችን ለመመለስ በትኩረት መሥራት ይገባል።