በኢትዮጵያ በተጨማሪ 179 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፡፡

182

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 07/2012 ዓ.ም (አብመድ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ4 ሺህ 845 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ179 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ ከተደረገላቸው ውስጥ ሰላሰው በአስከሬን ላይ የተካሄደ መሆኑን ያስታወቀው የጤና ሚኒስቴር በሁለት አስከሬን (አንድ ከጤና ተቋም እና አንድ ከማኅበረሰብ) ቫይረሱ እንደተገኘባቸው አመልክቷል፡፡ ሁለቱም ከአዲስ አበባ እንደሆኑም አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥርም 57 ደርሷል፡፡

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ዕድሜያቸው ከሁለት ወር እስከ 80 ዓመት የሚገኙ 116 ወንዶችና 63 ሴቶች ናቸው፡፡ ከ179 ሰዎች መካከል 176 ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡
ከዛሬዎቹ 111 ከአዲስ አበባ ናቸው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ 23 ከአማራ፣ 15 ከኦሮሚያ፣ 11 ከአፋር፣ 9 ከትግራይ፣ 5 ከሶማሌ፣ 2 ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እና 1 ከሐረሪ ክልሎች እንዲሁም ቀሪ 2 ሰው ደግሞ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንደሆኑ ተገልጧል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት ተጨማሪ 50 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎም 545 ደርሷል፡፡

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ 181 ሺህ 349 ሰዎችን መርምራ በ3 ሺኅ 345 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን አረጋግጣለች፤ የ57 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ 545 አገግመዋል፤ 2 ሺህ 741 ሰዎች ደግሞ በሕክምና ከትትል ላይ ናቸው፡፡ በጽኑ ሕሙማን ክፍል የነበሩት ሰዎች ቁጥር ወደ 30 ዝቅ ብሏል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleደቡብ አፍሪካ 1ሺህ 685 ፖሊሶች በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙባት አስታወቀች፡፡
Next articleከተማ አስተዳደሩ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ናሙና ለምርመራ እየወሰደ ነው፡፡