
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 07/2012 ዓ.ም (አብመድ) ደቡብ አፍሪካ የፖሊስ አገልግሎቷ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ችግር ውስጥ መውደቁን አስታውቃለች፡፡
ሀገሪቱ ዛሬ እንዳስታወቀችው እስካሁን 1ሺህ 685 ፖሊሶች በኮሮና ቫይረስ ተይዘውባታል፤ ከእነዚህ መካከል 14 ፖሊሶች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ 60ዎቹ ደግሞ አገግመው ወደ ሥራ ተመልሰዋል፡፡
ከአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛው የኮሮናቫይረስ ስርጭት የታየባት ደቡብ አፍሪካ እስከ ዛሬ ሰኔ 7/2012 ዓ.ም ድረስ 65 ሺህ 736 ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ አሳውቃለች፡፡ ሕይወታቸውን ያጡት ደግሞ 1ሺህ 423 መሆናቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ መላክታል፡፡
ምንጭ፡- ኒውስ 24 እና ሲ ጂ ቲ ኤን
በአስማማው በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡