
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 07/2012 ዓ.ም (አብመድ) በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 524 የላቦራቶሪ ምርመራ በ23 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ መኖሩ ታውቋል፡፡
ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ የተረጋገጡትም 20 ሰዎች ከመተማ ለይቶ ማቆያ፣ ሁለት ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ለይቶ ማከሚያ እና አንድ ከሰሜን ወሎ ላልይበላ ለይቶ ማከሚያ ናቸው።
በምርመራ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጡት ከ16 እስከ 52 ዓመት የዕድሜ ክልል የሚገኙ 21 ወንዶች እና ሁለት ሴቶች ናቸው፡፡ በአማራ ክልል እስከ ዛሬ ሰኔ 7/2012 ዓ.ም ድረስ ለ 4 ሺህ 966 ሰዎች የናሙና ምርመራ ተደርጎ በ198 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ለአብመድ አስታውቋል፡፡
በ24 ሰዓታት ውስጥ ሁለት ሰዎች ከባሕር ዳር ለይቶ ሕክምና መስጫ ማዕከል አገግመዋል፡፡ በክልሉ አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 39 ደርሷል፡፡
ትናንት በአማራ ክልል በጽኑ ሕሙማን የሕክምና ክፍል ገብቶ የነበረ ታማሚ ከጽኑ ሕሙማን ክፍል ወጥቷል። በክልሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ሕክምና መስጫ ማዕከል የሚገኙት ሁሉም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ቢሮው አስታውቋል።
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡