ልማት እና ሰላም የሚረጋገጠው በሕዝብ ትብብር ነው።

2
ደብረ ማርቆስ: ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ከደጀን ከተማ ነዋሪዎች እና የተቋማት መሪዎች ጋር በልማት እና በመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
በችግር ውስጥም ኾኖ በከተማው የተሠሩ የመሠረተ ልማት ተግባራት መልካም መኾናቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በተለይ ለከተማው ሕዝብ ከፍተኛ ችግር የነበረው የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት አሁን ላይ መሻሻል ማሳየቱንም አንስተዋል።
ነዋሪዎች በከተማ አሥተዳደሩ ሊሻሻሉ ይገባል ያሏቸውን ችግሮች ያነሱ ሲኾን መንግሥት ከተማዋን ለማልማት እና ለማሳደግ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ ነው የገለጹት፡፡
የደጀን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጤናው ደረሰ በችግር ውስጥም ኾኖ የማኅበረሰቡን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች የሚመልሱ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም የከተማው ሕዝብ የሚያነሳቸው የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት እንደሚሠራም ገልጸዋል።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋዬ በላይ ሰላም እና ልማት የሚረጋገጠው በሕዝብ ተሳትፎ መኾኑን አስገንዝበዋል። የከተማዋ ሰላም ዘለቂ እንዲኾን ሕዝቡ ተባባሪ እንዲኾንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ የከተማውን ሕዝብ ባሳተፈ መልኩ የተገነቡ መሠረተ ልማቶች የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል። የከተማ አሥተዳደሩ በዝቅተኛ ገቢ የሚኖሩ ዜጎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የሠራው ሥራ የሚደነቅ መኾኑንም ተናግረዋል፡፡
የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች እና ነዋሪዎች ለከተማዋ ዕድገት ላበረከቱት አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበምዕራብ ጎጃም ዞን በ15 ጤና ጣቢያዎች የላቦራቶሪ ግብዓት ለማሟላት እየተሠራ ነው።
Next articleአዳዲስ የበቆሎ ዝርያን በማውጣት ምርትን ለማሳደግ እየተሠራ ነው።