በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ሕዝባዊ የምክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

8

ጎንደር:12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በመድረኩ ከጎንደር ከተማ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ምሁራን እና ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።

ውይይቱ እያጋጠሙ ያሉ የሰላም ችግሮችን በማረም ሕዝብን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ የልማት ሥራዎችን ለማስቀጠል ያለመ ነው።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ያጋጠመው የፀጥታ ችግር በትምህርት፣ በጤና እና ሌሎች የልማት ሥራዎች ላይ ፈታኝ ችግሮችን ማስከተሉን ተናግረዋል። የሰላም እጦቱን በውይይት መፍታት ተገቢ መኾኑንም አንስተዋል።

ሰላም የሚጀምረው ከራስ ነው ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው መድረኩ ስለሰላም የጋራ ተግባራትን መከወን የሚያስችል መኾኑንም አስታውቀዋል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ አላምረው አበራ የተከሰተው የፀጥታ ችግር የሰው ልጅ ሕይዎት የቀጠፈ፣ ንብረትን ያወደመ፣ ተማሪዎች የትምህርት እድል እንዳያገኙ ያደረገ፣ የመድኃኒት አቅርቦት እና የጤና አገልግሎት ላይ ተፅዕኖ ያስከተለ ነው ብለዋል።

ከዚህ ችግር ለመውጣት እና ዘላቂ ሰላም ለመገንባት ከራስ መጀመር እና ለሰላም ባለቤት መኾን ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የሃይማኖት ተቋማት እና የሃይማኖት አባቶች ሰላምን ለመገንባት እየሠሩ ያሉትን ተግባር አድንቀው በቀጣይም ዘላቂ ሰላም እስኪረጋጥ ድረስ አስፈላጊውን ግንዛቤ እንዲፈጥሩ ጠይቀዋል።

ዘጋቢ፦ ኃይሉ ማሞ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የባሕር በር የሌላት ሀገር ሕዝብ፣ በር በሌለው ቤት ውስጥ እንደሚኖር ቤተሰብ ይቆጠራል” ኢትዮጵያዊው ካፒቴን
Next articleምሁራን ግጭትን ከምንጩ እንዲደርቅ የማድረግ ኀላፊነት አለባቸው።