ሕግን ያከበረ የነዳጅ ግብይት እንዲኖር እየተሠራ ነው።

3
ደብረ ማርቆስ: ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የነዳጅ አቅርቦት እና ስርጭት ላይ ይታዩ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
በከተማ አሥተዳሩ የሚገኙ 10 የነዳጅ ማደያዎች ሕጋዊ በኾነ አግባብ አገልግሎት እንዲሰጡ ግብረ ኀይል በማቋቋም የክትትል እና የቁጥጥር ሥራ እየተሠራ መኾኑንም የከተማ አሥተዳደሩ ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው ኀላፊ ዮሴፍ መለሰ በከተማዋ የሚገኙ አምስት የባጃጅ አሽከርካሪዎች ማኅበራት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር እንዲከተሉ በማድረግ መጉላላትን በሚቀርፍ መልኩ ነዳጅ እንዲቀዱ እየተደረገ መኾኑንም ገልጸዋል።
በነዳጅ ማደያዎች አካባቢ ይነሳ የነበረውን ሕገወጥነት ለመቆጣጠር አገልግሎቱን በቴሌ ብር አማካኝነት እንዲሰጡ ከመደረጉ በተጨማሪ በግብረ ኀይሉ አስፈላጊው ክትትል እና ቁጥጥር እየተደረገባቸው ስለመኾኑም ጠቁመዋል።
በተሠራው ውጤታማ እና የቅንጅት ሥራም የነዳጅ ማደያዎቹ ሥራቸውን በአግባቡ እንዲሠሩ ማድረግ ስለመቻሉ አብራርተዋል።
በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦት ችግር እንደሌለ የተናገሩት ኀላፊው ባለፉት ሦሥት ወራት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር በላይ ናፍጣ እና ከ 900 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ለተጠቃሚዎች ቀርቧል ብለዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ ከነዳጅ ግብይት ጋር የተያያዙ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ማሳየታቸውንም መምሪያው አስታውቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየሰላም እጦትን ለመፍታት የጋራ ሥራዎችን በአብሮነት መሥራት ያስፈልጋል።
Next articleየአርሶ አደሮች ቴክኖሎጅን የመጠቀም ፍላጎት ጨምሯል።