ከ33ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ እንደሚያለማ የሰሜን ጎጃም ዞን ገለጸ።

6

ባሕር ዳር: ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የዞኑን የመስኖ ልማት እና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ የንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

የዞኑ ምክትል አሥተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኀላፊ በለጠ ጥጋቡ በመስኖ ልማት እና በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ የንቅናቄ መድረክ ላይ ተገኝተው በዞኑ በ25 ዓመቱ አሻጋሪ የልማት እና ዘላቂ ዕቅድ የክልሉ ኢኮኖሚ 50 በመቶ የሚኾነው ከግብርና የሚገኝ ነው ብለዋል።

ይህንን ለማሳካት እና የክልሉን የአምስት ዓመት ዕቅዱን ለማሳካት በመስኖ እና ተፈጥሮ ሃብት ሥራ ላይ በትኩረት መሠራት አለበት ነው ያሉት።

በዚህም በዞኑ በ2018 በጀት ዓመት ከ33ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ እንደሚለማ ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ 21ሺህ ሄክታር የሚኾነው በበጋ መስኖ ስንዴ ይሸፈናል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ሰናይት በየነ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዶሮ ሃብት ልማት የወጣቶችን ሕይወት እየቀየረ ነው።
Next articleስለ ንግድ ምልክት ምን ያህል ያውቃሉ ?