የባሕር በር ጥያቄያችን የነበረንን እናግኝ ነው።

5

ሰቆጣ: ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ለአንዲት ሀገር ሁለንተናዊ እድገት የባሕር በር አስፈላጊ ነው። የባሕር በርን በማስመልከት አሚኮ ያነጋገራቸው የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎችም ለኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ጉዳይ የቅንጦት ጥያቄ አይደለም ብለዋል።

አቶ መልካሙ ደስታ የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ ናቸው። የባሕር በር ጥያቄያችን የነበረንን እናግኝ እንጅ አዲስ እናግኝ አይደለም ብለዋል።

አንዲት ሀገር የባሕር በር ከሌላት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ካሉ ሀገራት ጭምር እንድትለምን ትገደዳለች ያሉት ደግሞ አቶ አድህና ያለው ናቸው። ይህንንም በኢትዮጵያ አይተናል ያሉት አቶ አድህና የዛሬው ትውልድ በበሰለ መንገድ የባሕር በር ፍላጎትን ሊያሳካ ይገባል ብለዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጭ አቶ ንጉሤ ጌታሁን ደግሞ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ለያዘች ሀገር የባሕር በር መከልከል ከሞራል ውጭ መኾን ነው ይላሉ።

ይህ ጥያቄ የመንግሥት ብቻ ሳይኾን የመላው ኢትዮጵያውያን እንደኾነ ነው የገለጹት። ጥያቄው ምላሽ ያገኝ ዘንድ ሕዝቡ ውስጣዊ ሰላሙን መጠበቅ እና መንግሥትን መደገፍ ይገባዋል ነው ያሉት፤

በሕዳሴ ግድቡ የታየውን አንድነት በኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ላይ መድገም ያስፈልጋል ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ ለኢትዮጵያ እድገት በጋራ መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል ።

ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሴቶችን በልማት ኅብረት በማደራጀት በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው።
Next articleየዶሮ ሃብት ልማት የወጣቶችን ሕይወት እየቀየረ ነው።